$BTC #Write2Earn #EDUCATION #CRYPTO
🏔 የክሪፕቶ አለም ሚስጥራዊው አይስበርግ[የበረዶ ግግር]
Part 1.
🔖የክሪፕቶ አለም እንደ በረዶ ተራራ (iceberg) ነው። ለአብዛኛው ተጠቃሚ የሚታየው ከውሀው በላይ ያለው ትንሽ ክፍል ብቻ ነው። ለብዙሀኖቻችን አብዛኛው እና በጣም ወሳኙ ክፍሉ ግን ከውሃው በታች ተደብቋል። ይህ ምስል የክሪፕቶን አለም በሁለት ከፍሎ ያሳየናል፦ ከወገቡ በላይ ያለውና ከምድር በላይ የሚታየን ክፍል (ከውሃ በላይ) እና የተደበቀው ክፍል (ከውሃ በታች)።
🟢ከውሃ በላይ ያለው ክፍል (የሚታየው) 👁
✔️ይህ ክፍል አብዛኛው ሰው የሚያውቀው እና የሚጠቀምበት የክሪፕቶ ገጽታ ነው።
💸ቢትኮይን (Bitcoin) ₿: የክሪፕቶ አለምን የፈጠረው የመጀመሪያው ዲጂታል ገንዘብ ነው። ልክ የዚህ የበረዶ ተራራ ጫፍ ላይ እንዳለ ባንዲራ ሁሉ፣ ቢትኮይን የክሪፕቶን አለም የሚመራ እና የሚታወቅ ምልክት ነው።
💰አልትኮይኖች (Altcoins) 💠: ከቢትኮይን ውጪ ያሉ ሌሎች ክሪፕቶ ገንዘቦች በሙሉ Altcoins ይባላሉ። እነዚህም እንደ ኤቴሪየም (Ethereum)፣ ካርዳኖ (Cardano) እና ዶጅኮይን (Dogecoin) ያሉትን ያጠቃልላል። የየራሳቸው ዓላማና ጥቅም አላቸው።
💱📈🔥✖️💰📈📈💰🤑💰💰🦁📈📈🥞🦊💰👛👛ኤክስቼንጆች (Exchanges) 💱: እነዚህ በባህላዊው ገበያ ውስጥ ካሉት ባንኮች ወይም የአክሲዮን ልውውጥ መስሪያ ቤቶች ጋር ይመሳሰላሉ። ሰዎች ክሪፕቶን የሚገዙበት፣ የሚሸጡበት ወይም ወደ ሌላ ገንዘብ የሚቀይሩበት ዲጂታል ገበያዎች ናቸው።
✏️